Top

15

ፋየርቦል የኮምፒውተር ቫይረስ በዓለም ዙሪያ 250 ሚሊየን ኮምፒውተሮችን አጥቅቷል

Friday 9th of June 2017 07:40:11 AM  |  Fana Technology

ፋየርቦል የኮምፒውተር ቫይረስ በዓለም ዙሪያ 250 ሚሊየን ኮምፒውተሮችን አጥቅቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋየርቦል የተባለ እና በቻይና እንደተሰራ የተነገረለት አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 250 ሚሊየን ኮምፒውተሮችን ማጥቃቱ እየተነገረ ነው።

“ቼክፖይንት” የተባለ የመረጃ ደህንነት ተቋም እንዳስታወቀው፥ ተንኮለኛው ሶፍትዌር የተባለው ፋየርቦል የኮምፒውተር ቫይረስ የኢንተርኔት ብሮውዘሮችን የሚጠልፍ ነው።

ይህም የማፈላለጊያ ገጾችን እና ዋና ገጾችን በመቀየር የድረ ገጽ ትራፊካቸውን መቀመጫውን ቤጂንግ ካደረገው “ራፎቴክ” ለተባለው የዲጂታል ገበያ ኩባንያ በመከታተል የማስታወቂያቸውን በኔትዎርክ ላይ ይለቃል።

ራፎቴክ የተባለው ኩባንያ ብሮውዘሮችን የሚጠልፈውን እና የሀሰት የማፈላለጊያ ገጸ የሚያመጣውን ሶፍት ዌር መስራቱን ያልተቀበለ ሲሆን፥ በዓለም ዙሪያ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 300 ሚሊየን መድረሳቸውን ከማስተዋወቅም ተቆጥቧል ነው የተባለው።

ተንኮለኛው ሶፍትዌር በኮምፒውተራችን ላይ ኢንስቶል በሚሆንበት ጊዜ የተጠቃሚዎችን ብሮውዘር ከጎግል አሊያም ከያሆ ማፈላለጊያ ገጽ ጋር ተመሳስሎ ወደተሰራ ድረ ገጽ እንዲሄዱ ያደርጋል።

በዚህ ጊዜም የውሸት ደረ ገጹ የተጠቃሚዎችን መረጃ “ትራኪንግ ፒክስል” በተባለ ቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚሰበስብ መሆኑንም ቼክፖይንት ኩባንያ አስታውቋል።

እንደ ቼክፖይንት ገለጻ፥ ቫይረሱ በኩባንያዎች ውስጥ በተፈቀደላቸው ሰዎች ብቻ የሚከፈቱ ኮዶችን ከሩቅ ሆኖ ማንሰቃቀስ የሚችል ሲሆን፥ የተለያዩ ቫይረሶችን ኮምፒውተሮች ላይ በማውረድ (ዳወንሎድ) በማድረግ ተጠቃሚዎችን ማስቸገር እንደሚችልም ተገልጿል።

ለፋየርቦል ቫይረስ መጋለጣችንን እንዴት መለየት እንችላለን…?

የምንጠቀመው ኮምፒውተር ለፋየርቦል መጋለጥ ለአመጋለጡን ለመለየት የኢንተርኔት ብራውዘራችንን በመክፈት እነዚህን መልሶች መመለስ ብቻ በቂ ነው።

ዋና የኢንተርኔት ገጻችን (ሆም ፔጅ) በእኛ ነው የተከፈተው?፤ ማስተካከልስ እንችላለን?፣ ማፈላለጊያ ገጻችን አዲስ አልሆነብንም ማስተካከልስ እንችላለን?

ከእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ የአንዱ መልስ “እኔ አይደለውም” የሚል ከሆነ ይህ በቫይረሱ ለመጠቃታችን ምልክት ነው ተብሏል።

አንዴ በቫይረሱ ከተጠቃን በኋላ እንዴት አድርገን እናስወግድ…?

በራፎቴክ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ የማፈላለጊያ ገጾች “trotux.com፣ forestbrowser.com፣ luckysearch123.com እና ሌሎችም ናቸው፤ ማንኛውንም ከማስታወቂያ ጋር ተመሳስለው የሚመጡ ቫይረሶችን ለማስወገድ እነዚህን ቅደም ተከተሎች መከተል ይመከራል።

ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች

የዊንዶውስ ተጠቃሚዎች “አድዌሩን” ለማጥፋት ከፈለጉ ዊንዶውስ ኮንትሮል ፓናል ውስጥ ‘Programs and Features’ ላይ መተግበሪያውን ማጥፋት ይችላሉ።

ማክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለሚጠቀሙ

መተግበሪያውን ለማግኘት ማፈላለጊያ መጠቀም፤ በመቀጠልም የጠረጠርነውን “አድዌር” መተግበሪያ ወደ ትራሽ ውስጥ ስቦ ማስገባት ይመከራል። በመጨረሻም ትራሹ ባዶ እንዲሆን ማድረግ አለብን። እንዲሁም የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ኮምፒውተራችንን በየጊዜው ማጽዳትም ይመከራል።

ጎግል ክሮም ላይ

የክሮም ሜኑን (menu) ውስጥ Tools የሚለውን ከከፈትን በኋላ Extensions መምረጥ ከቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ናቸው ብለን የመረጥናቸውን (Add-ons) በሙሉ አንድ ላይ መምረጥ በመቀጠል የትራሽ ምልክትን በመንካት ሁሉንም ማጥፋት እንችላለን።

ሞዚላ ፋየርፎክስ ላይ

የሞዚላ ፋየርፎክስ ሜኑን (menu) መክፈት Tools tab ውስጥ መግባት በመቀጠልም ከሞዚላ ኤክስቴንሽን ውስጥ Add-ons በመምረጥ ማጥፋት።

በተጨማሪም የምንጠቀማቸው አንቲ ቫይረሶች ከምንጠቀመው ዳታ ቤዝ ጋር ተጣጥመው በትክክል መስራት አለመስራታቸውን ማረጋገጥ እና አፕዴት ማድረግ አለብን።

እንዲሁም በማስታወቂያ መልክ በነጻ የሚቀርቡልንን ሶፍትዌሮች ከመጠቀም መቆጠብ እንዳለብንም ይመከራል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :15     Down vote :0     Ajeb vote :15

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.