Top

15

ጎግል ሽብርን በሚያራምዱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን እቅድ ይፋ አደረገ

Monday 19th of June 2017 06:50:06 AM  |  Fana Technology

ጎግል ሽብርን በሚያራምዱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን እቅድ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ሽብርን የሚያራምዱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን ለመከላከል የሚያስችለውን ዝርዝር እቅድ ይፋ አድርጓል::

የሽብር አቋምን የሚያንጸባርቁ ቪዲዮዎች ማህበረሰቡ በፍርሃትና በስጋት በተሞላበት አኗኗር እንዲኖር የሚያስገድድ ስነልቦናዊ ጫና ይፈጥራሉ፡፡

አንዳንድ ሀገራት ሽብርን ለመዋጋት የሚያደርጉት ጥር ቢኖርም ብቻቸውን ስኬታማ ስራ ሊሰሩ ስለማይችሉ፥የግሉ ዘርፍም ሽብርን በመዋጋት ረገድ የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ለአብነትም ጎግል በዩቲዩብ ኩባንያው በኩል ሽብርን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ይጠቀሳል፡፡

የጎግል የቪዲዮ ማሰራጫ እና ማጋሪያ ገጽ ዩቲዩብ ለአጠቃቀም ቀላልና ማንኛውንም ቪዲዮ መጫን የሚቻልበት መሆኑ፥ ባለፉት ጊዜያት ሽብርን የሚያራምዱ በርካታ አቋሞች እንዲንጸባረቁበት ተገዷል፡፡

ጎግል በዚህ የቪዲዮ ማሰራጫ የቴክኖሎጂ ምዕራፉ የንግግር ነጻነት ወሰኑን እንዲያልፍ ምክንያት የሆነው ገደብ የሚጥሉ ህጎችን ወይም ፖሊሲዎችን ባለማዘጋጀቱ ነው፡፡

ሁኔታዎች እየከፉ በሽብር፣ ዘረኝነትና ፅንፈኛ አቋሞችን በሚያንጸባርቁ አካላት፥ የዓለም ማህበረሰብ ስነልቦናዊ ቀውስ ሲፈጠርበትና በኩባንያውም ላይ ግፊቶች ሲያድሩበት፥ ባለ አራት ክፍል ዝርዝር የሽብር ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች የሚከላከልበትን እቅድ ይፋ አድርጓል፡፡

ኩባንያው ከዚህም ባሻገር ከፌስቡክ፣ ትዊተር እና ማይክሮሶፍት ጋር ፅንፈኛ አቋም ያላቸውን የመረጃ ይዘቶች ለመቆጣጠርና ለመከላከል በጋራ እየሰራ ነው፡፡

የጎግል ኩባንያ ዋና አማካሪ ኬንት ወከር፥ በእርግጥ ሽብርን የሚራምዱ የቪዲዮ መረጃዎች ግልጽና ጠንካራ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ስኬታማ እንዳይሆን እያደረገ ሲሆን አንዱ ከሌላው ለማጋጨትም የሚጋብዙ መሆናቸው አሳሳቢ ነው ይላሉ፡፡

አሁን ከመንግስታት እና ከህግ አስፈጻሚ አካላት ጋር በመሆን እነዚህን ተግባራት ለመከላከል እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የቪዲዮ ይዘቶችን ለመቆጣጠርና ለመመርመር የሚስችሉ ዝርዝር ፖሊሲዎች የተዘጋጁ ሲሆን፥ በቀጣይም እያንዳንዱ የዩቲብ ገፅ ያለው አካል፥ የሚጭናቸው ቪዲዮዎች ተመርምረው ጉዳት የማያመጡ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ለህዝብ ተደራሽ ይናሉ ነው ያሉት፡፡

በተለይም በየዕለቱ የሚጫነው ቪዲዮ እጅግ በዙ ከመሆኑ የተነሳ፥ በበሰው ሃይልና በቴክሎጂ በመታገዝ የይዘት የማጣራት ስራዎችን ለመስራትም ታቅዷል ብለዋል፡፡

በእስካሁኑ የይዘት ምርመራ ሂደትም ኩባንያው 90 በመቶ ስኬታ እና ለስህተት ያልተዳረጉ ስራዎችን በሙከራ ደረጃ መስራቱ ተጠቁሟል፡፡

ጎግል በእቅዶቹ ውስጥ ለፖለቲካዊ ጥቅም ብቻ በጥላቻ የተመሰረቱ ንግግሮችን የሚያራምድ ቪዲዮን በይዘት ማጣራት ሂደት ፥ሙሉ ለሙሉ ማህበራዊ እና ሞራላዊ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ ከቪዲዮ ገጹ እንዲሰረዝ የማድረግ መርህን አካቷል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ሽብርን የሚያቀነቅኑ ቪዲዮዎችን ለመቀነስ ሚዛናዊ መረጃዎች እና በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የማያደርሱ ቪዲዮዎች ብዙ ማስታወቂያዎችን እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱም ተጠቁሟል፡፡

https://betanews.com

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :15     Down vote :0     Ajeb vote :15

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.