Top

20

የቀደሙ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች እና ባለ ክብረ ወሰኖች

Friday 10th of June 2016 11:06:49 AM  |  Fana News

 የቀደሙ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች እና ባለ ክብረ ወሰኖች

 ዛሬ ምሽት በስታድ ደ ፍራንስ የሚጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ ከተጠናቀቀው የአውሮፓ ሃገራት የውስጥ ውድድር በኋላ የትኩረት ማረፊያ ሆኗል።

የዛሬዋ አስተናጋጅ ፈረንሳይ ውድድሩ በ19 60 ሲጀመር የመጀመሪያ አስተናጋጅ የመሆን እድሉን አግኝታለች።

ውድድሩ ከዚህ ቀደም ለ14 ጊዜያት ያክል ሲካሄድ፥ ጀርመንና ስፔን ሶሰት ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

አስተናጋጇ ፈረንሳይ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ተከታዩን ደረጃ ይዛለች።

በእሰከዛሬው የውድድሩ ታሪክ ፈረንሳዊው ሚሼል ፕላቲኒ በ9 ግቦች የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ሲመራ፥ አለን ሺረር በ7 ጎል ይከተለዋል።

የቀደሙ የውድድሩ አሸናፊዎች፦

የመጀመሪያው የአውሮፓ ዋንጫ ባለ ታሪኮች የቀድሞዎቹ ሶቪየት ህብረት እና ዩጎዝላቪያ ናቸው።

በውድድሩ ፍጻሜ ተገናኝተው የአሁኗ ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ጨዋታውን 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አድርጋ ስማለች።

ተከታዩን የአውሮፓ ዋንጫ ያስተናገደችው ስፔን ደግሞ በፍጻሜው አብራት የቀረበችውን ሶቪየት ህብረትን 2 ለ 1 በማሸነፍ ቤቷ አስቀርታዋለች።

ጣሊያን ተከታዩን የአውሮፓ ዋንጫ አስተናግዳ ስታስቀር፥ ከሁለት ከተለዩ ጀርመኖች በጠንካራነቱ የዘለቀው ምዕራብ ጀርመን ቡድንም ተከታዩን ውድድር ማሸነፍ ችሏል።

የቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ (አሁን ቼክ ሪፐብሊክ እና ስሎቫኪያ በመባል ሁለት ሀገር ሆናለች) ቀጣዩን የአውሮፓ ዋንጫ ማሸነፍ ችላለች።

ተከታዩን ደግሞ ጠንካራዋ ምዕራብ ጀርመን ስታሸንፍ፥ ፕላቲኒ በነገሰበት እና ሃገሩ ባስተናገደቸው የአውሮፓ ዋንጫ ለስ ብሉሶቹ አሸናፊ ሆነዋል።

በማርኮ ቫንቫስተን ፊት አውራሪነት የተመሩት፥ ብርቱካናማዎቹ ሆላንዶች ደግሞ በ19 88 በምዕራብ ጀርመን አስተናጋጅነት የተዘጋጀውን የአውሮፓ ዋንጫ አሸንፈዋል።

በ19 92 የስዊድኑ የአውሮፓ ዋንጫ ደግሞ ከውድድሩ ውጭ የነበረችው ዴንማርክ በውድድሩ ማጣሪያ ከምድቡ ያለፈችውን ዩጎዝላቪያን ተክታ በመሳተፍ አሸናፊ ሆናለች።

በወቅቱ ዩጎዝላቪያ በሃገሯ በተፈጠረው ቀውስ እና ጦርነት ምክንያት ከውድድሩ መሰረዟ ይታወሳል።

የዴንማርክ ብሄራዊ ቡድንም ሳይታሰብ ጠንካራውን ጀርመንን አሸንፎ የውድድሩን የአሸናፊነት ዘውድ ደፍቷል።

ተከታዩን ውድድር ደግሞ ከውህደት በኋላ ጀርመን ስታሸንፍ፥ ፈረንሳይ ዩሮ 2000ን ማሸነፍ ችላለች።

የፖርቹጋሉን የአውሮፓ ዋንጫ ደግሞ የኦቶ ሬሃግሏ ግሪክ፥ በአምበሏ ቴዎድሮስ ዛጎራኪስ መሪነት ዋንጫውን መሳም ችላለች።

ከዛ በኋላ የተዘጋጁትን ያለፉትን ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ደግሞ የጊዜው ሃያል የነበረችው የእነ ዣቢ ስፔን አሸንፋለች።

ይህ የስፔን የተከታታይ ድል ደግሞ በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ብቸኛውና የመጀመሪያው ነው።

ለፍጻሜ በተደጋጋሚ የቀረቡ፦ ጀርመን ከውህደት በፊትና በኋላ አጠቃላይ ስድስት ጊዜ በመቅረብ ቀዳሚዋ ናት።

ስፔን ደግሞ አራት ጊዜ በመቅረብ ትከተላለች።

በጭማሪ ሰዓት የተጠናቀቁ ጨዋታዎች፦ የ19 68 የጣሊያን የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ በጣሊያንና ዩጎዝላቪያ ሲካሄድ በመልስ ጨዋታ ነበር የተጠናቀቀው።

በመጀመሪያው 1 ለ 1 የተለያዩት ሁለቱ ተፋላሚዎች በመልሱ ጨዋታ የጣሊያን ቡድን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

የእንግሊዙ 19 96 የአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜም በጀርመንና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል ሲካሄድ በወርቃማ ጎል ነበር የተጠናቀቀው፤ ኦሊቨር ቢዬርሆፍ ጎል አስቆጣሪው ነበር።

ሆላንድና ቤልጂየም ያስተናገዱት ዩሮ 2000 ፈረንሳይ ጣሊያንን ያሸነፈችው ዴቪድ ትሪዝጌት ባስቆጠረው የጭማሪ ሰዓት ጎል ነበር።

ከዛ ውጭ በ19 76 በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተስተናገደው የአውሮፓ ዋንጫ በመለያ ምት ተጠናቋል።

ውድድሩን የቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ ምዕራብ ጀርመንን በመለያ ምት 5 ለ 3 አሸንፋ ዘውዱን ደፍታለች።

በውድድሩ የፍጻሜ ታሪክ በሰፊ የጎል ልዩነት የተጠናቀቀው ጫዋታ ደግሞ ፖላንድና ዩክሬን ያዘጋጁት ያለፈው የአውሮፓ ዋንጫ ነው።

በውድድሩ ለፍጻሜ ስፔን ከ ጣሊያን ቀርበው ስፔን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

ዛሬ ምሽት በፓሪስ ሲከፈት 24 ሃገራት ለዋንጫው ይፋለማሉ፥ ብልጭ ድርግም የሚለው የፀጥታ ሁኔታም ከዘንድሮው ውድድር ጋር አብሮ የሚነሳ ጉዳይ ነው።

የስፔን ብሄራዊ ቡድን ተሳክቶለት ይህን ውድድር ካሸነፈም በአውሮፓ ዋንጫ ውድደር የራሱን ታሪክ ያሻሽላል፤ በተከታታይ 3 ጊዜ በማሸነፍ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ (6)፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች (6) እና ዋይኒ ሩኒ (5) ፥ ተጨማሪ ጎል ካስቆጠሩ የፕላቲኒን ክብረ ወሰን ለመጋራት እድሉን ያገኛሉ።

 

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.