Top

18

አባ ማቲያስ:- ከመሳሳም ይቅርታ ይቅደም!

Saturday 5th of March 2016 03:03:00 PM  |  Deje Selam


Varican%2BKisses.jpg·        "ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው" (አባማቲያስሕዳር 2008) ·        " ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?) እንመልሰዋለን" (አባማቲያስየካቲት 2008) ·         " ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝ ገዥ ነው" (አባማቲያስጥቅምት 2008) ·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ--- አባት ብሎ ዝም!!
(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝት ማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይ " ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው" በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል:: http://www.addisadmassnews.com/images/Issue-826.pdf


ሀገራዊ ማህበራዊና ብሔራዊ በሆነ ጉዳይ ላይ " አንተ ኦርቶዶክስ : አንተ ካቶሊክ" መባባሉ ሳይኖር የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም እንዳለበት ግልጽ ነው:: "ኦርቶዶክስና ካቶሊክ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ነው" ብሎ የማይመስል ነገር መናገሩ ( ያውም ከፓትርያርኩ አንደበት) ግን እጅግ የሚያስተዛዝብና ግምት ውስጥ የሚጥል ስህተት ነው:: የሆነው ሆኖ ይህን ባሉ በሶስተኛው ወር የካቶሊኳ ራስ ቫቲካን ደርሰው የበርካታ ኢትዮጵያውያንን አንጀት አቁስለው ተመልሰዋል::
 ፓትርያርኩ ቫቲካን መሄድ ነበረባቸውን?
በመሰረቱ: ቫቲካን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እጅግ የመረረ ግፍ ፈጽማለች:: ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር : የቫቲካን ጳጳሳት የመርዝ ጋዝ እየባረኩ ኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደሆነ አውጀዋል:: የወርቅ መስቀላቸውን ሳይቀር ለጦርነቱ አዋጥተዋል:: የሙሶሎኒምና የግራዚያኒ ቀኝ እጅ የነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ ባደባባይ ወረራውን ደግፎ መግለጫ ሰጥቷል::
(http://www.globalallianceforethiopia.org/italianinvasion.pdf)
ፋሺስት ጣልያን አንድ በዛ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድላለች:: በሺዎች የሚቆጠሩ ካህናትን አቃጥላለች:: በውል የታወቁትን እንኳን ብንቆጥር ወደ 2 ቪህ አብያተ ክርስቲናትን አውድማለች:: ጣልያን ከመውረሯ በፊትም የጣልያን ሰላይ እየሆኑ ይሰሩ የነበሩት የቫቲካን መነኮሳት ነበሩ::
ቫቲካን ስለሰራችው ጥፋት ኢትዮጵያንን እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ስላልሆነች : ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የቫቲካንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ቫቲካን ይቅርታ እስካልጠየቀች ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባቶች ከቫቲካን ጋር አንድነት እንዳይኖር በመወሰናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ( የአለቃ አያሌው " መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና" መጽሓፍን ይመልከቱ)
በተለይ አሁን በቅርቡ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ ጣልያን ውስጥ ሀውልት እንዲቆም ከተወሰነ በኋላና የቫቲካን ጳጳሳትም ይህን ጉዳይ የመደገፋቸው ዜና በመሰማቱ : በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በማሰማታቸው የሃውልቱ ስራ ቆሟል:: እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቫቲካን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ቢወተውቱም : ቫቲካን ካላት ንቀት የተነሳ ፈቃደኛ አልሆነችም:: የሙገርመው ግን " የ ጀርመን ናዚዎች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ዝም በማለቴ ( ባልሳተፍበትም) ይቅርታ ጠይቃለሁ" ብላ አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች::
(https://www.gopetition.com/…/vatican-apology-for-ethiopian-…)
ራሷ የጨፈጨፈችውንና ያስጨፈጨፈችውን ኢትዮጵያውያንን ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ : ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እስክትጠይቅ ድረስ ይፋዊ ግንኙነት እንዳይኖር በኢትዮጵያ በኩል ተወስኖ ነበር:: የአለቃ አያለውውን መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ያነቧል::
አባ ማቲያስ ግን ያንን እግድ ጥሰው ቫቲካን ድረስ በመሄድ " እኛና ቫቲካን ድሮም ፍቅር ነን: የድሮውን ፍቅር እንመልሰዋለን " በማለት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ድካም መና አብልተውታል::
የአባ ማቲያስ ቫቲካን መሄድ እንግዳ ቢሆንም ብዙዎ " እዛው ሀገራቸው ላይ ሄደው ቫቲካን ለሰራችው በደል ይቅርታ ትጠይቅ" ብለው ይናገራሉ ተብሎ ተጠብቆም ነበር:: በተገላቢጦሹ ግን አባ ማቲያስ " ድሮም እኛና ቫቲካን ፍቅር ነበርን ወደፊትም ያንን ፍቅር እንመልሰዋለን" ብለው አረፉት::
የቀደመው የቫቲካንና የኦርቶዶክስ ፍቅር የቱ እንደሆነ አልገባኝም:: የዲዮስቆሮስ ይሆንን? ከጥንት ጀምሮ ቫቲካን የምትልካቸው ሚሺነሪዎች ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ነገር ሲተክሉ እንጂ ፍቅር መስርተው ሲሄዱ አይታወቅም:: እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን መጥቀስ ይቻላል:: ቃል በቃል " ኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ ሁለት እሾክ ተክዬባት ሄድኩ" እስከማለት የደረሱ ናቸው:: ጸጋና ቅባትን ያስትውሷል:: ነ ጂሴፔ ሳፔቶና አባ ማስያስም ኢትዮጵያን ለጋ ቅቤ ሲቀቡ አናቃቸውም:: በሁለቱም የጣልያን ጦርነት ወቅትም ቫቲካን የሰራችው ወንጀል እንጂ የፍቅር ስራ አይደለም:: (አቡነ ጎርጎርዮስ የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ታሪክ)
የኦርቶዶክስና የቫቲካን የቀደመ ፍቅር የቱ እንደሆን አይገባኝም:: ፓትርያርኩ እንደዛ ከሚሉ " ቫቲካን አትፍታለችና ይቅርታ ትጠይቅ" የ,ኢለውን ያባቶቻቸውን ቃል አጽንተው እሳቸውም ይሄን ቢያደርጉ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም ታሪክ ነበር:; ማኅበረ ቅዱሳንን " ቅኝ ገዥ" ያለ አንደበት እውነተኛዋ ቅኝ ገዥን ምን ይላት ይሆን ብዬ ጠብቄም ነበር::
ምን ያደጋል ! አባታችን አገላበጡት

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :18     Down vote :0     Ajeb vote :18

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.