Top

19

አይረሴው አትሌት ወርቁ ቢቂላ

Saturday 30th of August 2014 10:18:50 AM  |  Addis Admas Sport

“አትሌት የሆንኩት ባለማወቅ ካዳበርኩት አቅም ነው” አትሌት ወርቁ ቢቂላ ወርቁ ቢቂላ በጣም ታዋቂና አይረሴ የሚያሰኙ በርካታ የአትሌቲክስ ገጠመኞች ያሉት ታዋቂ አትሌት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ከ1976 ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ 2002 ድረስ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የአገሩን ባንዲራ በድል አ…

19

የምስራቅ አፍሪካ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ይካሄዳል

Saturday 23rd of August 2014 10:51:01 AM  |  Addis Admas Sport

                 የምስራቅ አፍሪካ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በሚገኘው ዘመናዊ ጅምናዚዬም በነገው እለት ሊጀመር ነው። ውድድሩን ዓለምአቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን (IHF) የሚያዘጋጀው ሲሆን በአፍሪካ ደረጃ በዞን አምስት የሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሌና ሱዳን ይሳተፉበታል፡፡ አ…

19

የአውሮፓ 5 ታላላቅ ሊጎች በ2014 - 15

Saturday 16th of August 2014 11:16:37 AM  |  Addis Admas Sport

     ብራዚል ካዘጋጀችው 20ኛው ዓለም ዋንጫ 1 ወር ካለፈ በኋላ የዓለም ስፖርት አፍቃሪ ትኩረት ወደ አምስቱ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ዞሮ ቆይቷል፡፡ አምስቱ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፤ የስፔን ፕሪሚዬራ ሊጋ፤ የጀርመን ቦንደስ ሊጋ፤ የጣሊያን ሴሪኤና የፈረንሳይ ሊግ 1 ሲሆኑ በሚቀጥሉት 9

19

እግር ኳስ የቢሊዬነሮች መናሐርያ ሆኗል

Saturday 16th of August 2014 11:15:51 AM  |  Addis Admas Sport

ባለፉት 10 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ የቢሊዬነሮች ሚና እና የኢንቨስትመንት ድርሻ እያደገ መጥቷል፡፡ በተለይ በአውሮፓ አምስት ታላላቅ ሊጎች   በቢሊዬነሮች ሙሉ ለሙሉ በባለቤትነት በመያዛቸውና በከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ኢንቨስት ስለተደረገባቸው  የፉክክር ደረጃቸውን ያሳደጉ ከ10 በላይ ክለቦች ናቸው፡፡…

19

በ23ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ

Saturday 16th of August 2014 11:14:40 AM  |  Addis Admas Sport

20 ክለቦች ፤ 5.3 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ 516 ተጨዋቾች   በተጨዋች ስብስብ ውዱ ክለብ — ማን ሲቲ 647.7 ሚሊዮን ዶላርውዱ ተጨዋች —  የማንችስተር ሲቲው ኤዲን ሃዛርድ በ63.84 ሚሊዮን ዶላርበ84ኛው የስፔን  ፕሪሚዬራ ሊጋ20 ክለቦች 4.01 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ 491 ተጨዋቾች በተጨዋች ስብስብ ውዱ ክለብ —ሪያል ማድሪድ 953.61

19

የተራራ ሩጫ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው

Saturday 9th of August 2014 12:00:45 PM  |  Addis Admas Sport

               በአቢያታና ሻላ ሃይቆች ተራራማ ስፍራዎች ዙሪያልዩ  የሩጫ ውድድር መዘጋጀቱን አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም አስታወቀ፡፡  
የተራራ  ሩጫው ነሐሴ 11  በአብያታና ሻላ ሃይቆች ዙሪያ ሲካሄድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሚሆን የውድድሩ አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡ ኢትዮ ትሬል 2014 (Ethiotrail) በሚል በሦስት የውድድር መደቦች ስያሜ የሚካሄደው የተራራ ሩጫው የ42 ኪ.ሜ፣ የ21 ኪ.ሜ የ12 ኪ.ሜ ውድድሮች ይኖሩታል፡፡ አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም የተራራ ሩጫው ከዚህ በፊት በጐዳና እና በትራክ ውድድሮች ተወስኖ ለነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አንድ ተጨማሪ የውድድር ዕድል  ይፈጥራል፡
በተራራ  ሩጫው በ42 ኪ.ሜ፣ በ21 ኪ.ሜ እና በ12 ኪሎሜትር ውድድሮች ከ250 በላይ ተሳታፊዎች ይኖራሉ፡፡ 165 ያህሉ ከ10 አገራት (ከአሜሪካ፣ ቺሊ፣ ፖላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ካታሎና) የመጡ እንደሆኑ አዘጋጆች ገልፀው ፤ እነዚህ ስፖርተኞች ተሳትፎ እንዲያደርጉ አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም ለ2 ወራት ለመላው አውሮፓ በመዘዋወር ቅስቀሳ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
አራት አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሐናት ለውድድሩ ሽፋን የሚሰጡት ሲሆን ሱፕር ስፖርት እና ታዋቂው የሯጮች መጽሔት ራነርስ ዎርልድ ይገኙበታል፡፡
በዚህ የተራራ ሩጫ ላይ የሚሳተፉና የሚያሸንፉ አትሌቶች በተለይ  ከ1-5 ደረጃ የሚያገኙት በዓለም አቀፍ ውድድር እንዲሳተፉ እቅድ መኖሩንም አውቋል፡፡
በውድድሩ አዘጋጅነት ከሠራው አይአርአይ ጋር የምስራቅ አፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ኔትዎርክ (HORECK) እና የብሔራዊ ፓርኮች ጥበቃና አስተዳደር የሆነው የመንግስት ተቋምና የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ በአጋርነት ተሳትፈዋል፡፡  ውድድሩ ለአትሌቶች ከሚፈጥረው ተጨማሪ የውድድር እድል ባሻገር ለዘላቂ ልማት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፍና የቱሪዝም አገልግሎትን ለማስተዋወቅ ምቹ መድረክ ነው ተብሏል፡፡
የብሔራዊ ፓርኮች ጥበቃና አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የተራራ ሩጫው በአቢያታ እና ሻላ ሃይቆች ዙርያ ለሚገኘው ብሄራዊ ፓርክ ህልውና የሚያግዝ ብለውታል፡፡ ብዙዎቹ የአገሪቱ ብሄራዊ ፓርኮች በከፍተኛ ተራራማ ስፍራዎች ላይ መገኘታቸው ተመሳሳይ የስፖርት ውድድሮች በብዛት ለማካሄድ ይጠቅማል ያሉት አቶ ኩመራ፤ ለአገር ገጽታ ግንባታ ትልቅ ሚና የሚጫወት ጥሩ  ውድድር ነው ብለዋል፡፡
የተራራ ሩጫውን ለማዘጋጀት ለ1 ዓመት ተኩል እንቅስቃሴ መደረጉን የገለፁት አዘጋጆቹ ዓለምአቀፍ ደረጃ ማሟላቱን ለመፈተሽ ከስፔን አገር ለውድድሩ ዓይነት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎች 3 ጊዜ ተመላልሰው ጥናት አድርገዋል ብለዋል፡፡

19

በመጨረሻም ዋልያዎቹ ብራዚል መሄዳቸው አልቀረም

Saturday 9th of August 2014 11:58:51 AM  |  Addis Admas Sport

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ የብራዚል ጉዞ  በ20ኛው ዓለም ዋንጫ  ተሳትፎ  ባይሳካም፤ ለሁለት ሳምንት ዝግጅት መሄዳቸው አልቀረም፡፡
በአሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ጥረት በብራዚል በካምፕ በአይነቱ የተለየ ዝግጅት የሚያደርጉት ዋልያዎቹ በ20ኛው ዓለም ዋንጫ  ተሳታፊነት ብራዚልን በመርገጥ አስደናቂ ብቃት ያሳየችውን አልጄርያ ከመግጠማቸው በፊት ጥሩ ብቃት ላይ እንደሚደርሱ እየተነገረ  ነው፡፡ ከብራዚል ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው ብሄራዊ ቡድኑ  በቆይታው የሚያገኘው ጥቅም ያመዝናል። አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ቋሚ ተሰላፊ ቡድናቸውን ለመለየት ያሰቡ ይመስላል፡፡ ባሬቶ በሃላፊነቱ በቆዩባቸው ጊዜያት ቋሚ አምበል አለመሾማቸው ሙሉ ቋሚ ተሰላፊዎች አለመለየታቸውን ያመለክታል፡፡ ፍቅሩ ተፈራ፤ አበባው ቡጣቆ እና ፍፁም ገብረማርያም አምበሎች እንደሚሆኑ እየተገመተ ነው፡፡ አዳነ ግርማ፤ ሳላዲን ሰኢድና መስኡድ መሃመድም ለሃላፊነቱ ብቁ መሆናቸውም ይገለፃል፡፡ 19 አባላትን ያካተተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  የመጀመርያው ልዑክ ረቡዕ ወደ ብራዚል ተጉዟል፡፡ ቀሪዎቹ ዛሬ ይበራሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በብራዚል በሚኖረው የ14 ቀናት ቆይታ 33 አባላት ያሉት ልዑክ ይኖረዋል። በብራዚሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከሰሜን ብራዚል ከመጣው ሬምዋ ከተባለ ክለብ ይጫወታል፡፡ የዛሬ ሳምንት ደግሞ በ20ኛው ዓለም ዋንጫ ጨዋታ አስተናግዶ በነበረው የማኔ ጋሪንቻ ስታድዬም ሁለተኛውን ጨዋታ ያደርጋል፡፡  ከ2 ሳምንት በኋላ  ደግሞ ሬዮ ግሬምዬ ከተባለ ክለብ ጋር ሶስተኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል፡፡ ሦስቱም የብራዚል ክለቦች በአገሪቱ የክለብ ውድድር በ4ኛ ዲቪዚዮን የሚጫወቱ ናቸው፡፡ ጨዋታዎቹ አቋምን ከመፈተሽ ባሻገር ተጫዋቾቹን ለማስተዋወቅ ጥሩ እድል እንደሚፈጥር አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ተናግረዋል፡፡
በ2015 እኤአ ላይ ሞሮኮ ለምታስተናግደው 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚካሄድ  የምድብ ማጣርያ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር  ከመጫወቱ በፊት ቢያንስ ስምንት የወዳጅነት ጨዋታዎች ሊያደርግ ይችላል፡፡ ዋልያዎቹ ባለፈው ሰሞን  በሉዋንዳ ላፓላንካ ኔግራስ ከተባለው የአንጎላ ብሄራዊ ቡድን ጋር በመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታቸው ተገናኝተው 1ለ0 ተሸንፈዋል፡፡
በሉዋንዳ 11 ዲ ኔቨምብሮ ስታድዬም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንጎላ ያሸነፈችው ፍሬዲ የተባለ ተጨዋች በ16ኛው ደቂቃ ላይ ባገባት ብቸኛ ግብ። የአንጎላው ፕሬዝዳንት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶሳንቶስ የክብር እንግዳ ነበሩ፡፡
ከብራዚል መልስም  በነሀሴ ወር ሁለት የደርሶ መልስ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ፈርኦኖቹ ከተባለው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለማድረግ ቀጠሮ መያዙም አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ 2 የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታው ጳጉሜ 2 ላይ በአዲስ አበባ ስታድዬም ከአልጄርያ  ይገናኛል፡፡ አልጄርያና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ እና ዋና ውድድሮች 6 ጊዜ ተገናኝተዋል። እኩል አንዴ ተሸናንፈው በ4 ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል፡፡ በምድብ 2 ከአልጄርያ፤ ከማሊ እና ከኢትዮጵያ ጋር ማጣርያ የምትገባው አራተኛ ቡድን ማላዊ ሆናለች፡፡ ማላዊ ምድቡን የተቀላቀለችው በሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣርያ ቤኒን ጥላ በማለፍ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የሴካፋ ዋና ፀሃፊ ኒኮላስ ሙንሶኜ በሞሮኮው 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመካከለኛው እና የምስራቅ ዞን አንድ ተወካይ መኖሩ አይቀርም ብለዋል። ከዞኑ አራት ቡድኖች በምድብ ማጣርያው የሚካፈሉ ሲሆን ኢትዮጵያ እና ሱዳን በቀጥታ ወደ ምድብ ሲገቡ በቅድመ ማጣርያ ያለፉት ደግሞ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በማጣርያ  በሜዳዋ በምታደርጋቸው ጨዋታዎች ባለፈው ሁለት ዓመት ያሳየችው ብቃት ለጥንካሬዋ ምክንያት እንደሚሆን ኒኮላስ ሙንሶኜ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከወራት በኋላ የመካከከለኛው እና ምሰራቅአፍሪካ ሻምፒዮና አዘጋጅ እንደሆነች ይታወቃል።

19

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ‹‹ውዱ›› ተጨዋች ፤ ዳዊት እስጢፋኖስ

Saturday 9th of August 2014 11:57:23 AM  |  Addis Admas Sport

ሰሞኑን ባልተጠበቀ የአስተዳደር ችግር እየተናጠ ያለው ኢትዮጵያ ቡና በካጋሜ ካፕ አለመሳተፉ ትልቅ ኪሳራ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በክፍለ አህጉራዊው የክለቦች ሻምፒዮና  ያልተሳተፈበት ምክንያት ከተፈጠረው ችግር ከተያያዘ የሚያሳዝን ነው፡፡ ካጋሜ ካፕ የክለቡን ብራንድ የሚያሳድግ ውድድር ነበር፡፡ ለሚቀጥለው የፕሪሚዬር ሊግ የውድድር ዘመን ከፍተኛ መዘጋጂያ ሊሆን የሚችልም ነበር፡፡
የ27 ዓመቱ ዳዊት እስጢፋኖስ በአማካይ ተጨዋችነት ምርጥ ከሚባሉ ዋልያዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና አምበል እና ወሳኝ ተጨዋች ሆኖ የሚያገለግለው ዳዊት፤ ከዋልያዎቹ ጋር ወደ ብራዚል የመሄድ እድል አልገጠመውም። በጉዳት ላይ ሲሆን እያገገመ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ የሚያቀርበው ዳዊት ዋልያዎቹ ከማርያኖ ባሬቶ ጋር እየሰሩ ያሉት ዝግጅት ከሞላ ጎደል ጥሩ ብሎታል፡፡ በተጨዋቾች ዝውውር ገበያ ደህና ክፍያ መሰማቱን ደግሞ የስፖርቱ እድገት መገለጫ መሆኑን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዳዊት እስጢፋኖስን ለቀጣይ 2 ዓመት ኮንትራቱን እንዲያራዝም የከፈለው 1.2 ሚሊዮን ብር ነው ፡፡  በኢትዮጵያ እግር ኳስ የተጨዋቾች ዝውውር ገበያ አዲስ ሪኮርድ የፊርማ ሂሳብ ተብሏል፡፡  የብሄራዊ ቡድን ተጨዋች  አይናለም  ሃይሉ ከዓመት በፊት ከደደቢት ክለብ ወደ ዳሸን ቢራን የተቀላቀለበት  1.1 ሚሊዮን ብር ቀድሞ የተመዘገበው ሪከርድ ክፍያ  ነበር፡፡
ከውጭ አገር ክለቦች የባርሴሎና  እና አርሰናል ክለቦችን አደንቃለሁ የሚለው ዳዊት እስጢፋኖስ በእረፍት ጊዜው ከብዙ ጓደኞቹ ጋር ተሰባስቦ በሁሉም ጉዳይ መጫወት ያስደስተኛል ብሏል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፊልሞችን በመከታተል እየተመለከተ ነው፡፡
ዳዊት እስጢፋኖስ ከስፖርት አድማስ ጋር ያደረገው አጭር ቃለምልልስ ከዚህ በታች የቀረበው ነው፡፡    
ስለ ኢትዮጵያ ቡና ወቅታዊ ሁኔታ
ለማንም ወገንተኛ በመሆን የምናገረው ነገርየለም። እኔም የቡና ነኝ ፤እነሱም የቡና ናቸው፡፡ የሁላችንም ለሆነው ታላቅ ክለብ ብለው በቶሎ ያለባቸውን ልዩነት አጥብበው በቶሎ መስማማታቸውን በጉጉት እጠብቀዋለሁ፡፡
ስለ የአሁኑ ብሄራዊ ቡድንና ማርያኖ ባሬቶ
 ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በሰራሁባቸው ቀናት የታዘብኩት በጣም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደምንገኝ ነው፡፡ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶን በሁለት ነገር አደንቃቸዋለሁ። በቡድኑ ተጨዋቾች የአካል ብቃት ላይ በማተኮር መስራታቸው ለውጥ ነበረው፡፡ በሌላ በኩል የወዳጅነት ጨዋታዎችን መተግበር የቻሉ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ አስቀድሞ በነበረው የብሄራዊ ቡድን ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታዎች ብዙም የሚሳኩ አልነበሩም፡፡
በአጠቃላይ በታክቲክ እና በአካል ብቃት የሚሰሩ ስልጠናዎች እድሜያቸው ለገፋ 25 እና ከዚያም በላይ ለሆኑ ተጨዋቾች በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ለመስራት አድካሚ ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ከታዳጊዎች ተነስቶ በመስራት በሁለት እና ሶስት ዓመት ለውጥ የሚታይበት ነው፡፡ ይህ ቡድን በጣም አብሮ የቆየ ነው፡፡ በመሰረታዊ ነገር መጎተት የለበትም፡፡ የወዳጅነት ጨወቃታዎቹን በተመለከተ ግን እሰከዛሬ የማይሳካው አሁን መገኘቱ ጥሩ ርምጃ ነው፡፡ ለወደፊቱ ግን የወዳጅነት ጨዋታዎቹ በጥናት መደረግአለባቸው፡፡ በገባንበት ፉክክር በሚገጥሙን ቡድኖች አቋም እና የኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ያላቸውን አቅም ተተንተርሶ የወዳጅነት ጨዋታ መዘጋጀት አለበት፡፡ የተጋጣሚ አገር ሜዳ እና የራስ ሜዳ ሁኔታ እና አየር በማጥናት የሚደረግ ዝግጅትን የሚያግዝ የወዳጅነት ጨዋታ ያስፈልጋል፡፡
ስለ ምድብ 2
የምድብ ማጣርያው ላለፈውአፍሪካ ዋንጫ ከነበረው ድልድል ይከብዳል፡፡ በራሳችን አጨዋወት ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን እንችላለን፡፡ በተለይ በሜዳችን ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች ትኩረት መስጠት አለብን፡፡ በጠንካራ ብሄራዊ ስሜት በመስራት ውጤታማ ለመሆን የተነሳሳን ይመስለኛል፡፡ በስነልቦና የምናደርገው ዝግጅትም ወሳኝ ይሆናል፡፡
ስለ ተጨዋቾች የዝውውር ገበያ
ከቅርብ ዓመታትወዲህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማደጉ በተለያየ መንገድ ይገለፃል፡፡ አንዱ መገለጫ ደግሞ የተጨዋቾች የዝውውር ገበያው በከፍተኛ ሂሳብ መካሄዱ ነው፡፡ ካለፉት አራትአመታት ወዲህ ተጨዋቾች በብቃታቸው ተፈላጊ ሆነው ከክለብ ወደ ክለብ ለመዘዋወር የሚያገኙት የፊርማ ሂሳብ ተጠቃሚ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡ተጨዋቾች በክለባቸው ልምምድሰርተው በግላቸውም ብቃታቸውን ለማሳደግ የሚጥሩበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ 1 ሚሊዮን ብር እየተከፈለ ማንም የሚተኛ የለም፡፡ የስፖርቱ እድገት በኢኮኖሚ በሚኖሩ መሻሻሎች የሚፋጠን ይመስለኛል፡፡


19

ሳይንስና ቴክኖሎጂ የእግር ኳስን ተፈጥሮ ይለውጣሉ!?

Saturday 2nd of August 2014 11:11:58 AM  |  Addis Admas Sport

         ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በስፖርቱ ላይ አዎንታዊም አሉታዊም ሚና ይኖራቸዋል፡፡ የተሻለ ለውጥ ወይም የባሰውን ውድቀት ይፈጥራሉ፡፡ በዓለም ዙርያ በርካታ ስፖርት አፍቃሪዎች እግር ኳስ በቀላል እና ተፈጥሯዊ ባህርያቱ እንዲቀጥል ቢፈልጉም፤ የስፖርቱ ባለሙያዎች በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መታጀቡ የእድገት መገለጫ ነው ብለው ይከራከራሉ፡፡ በአውሮፓ እግር ኳስ የሚሰሩ በርካታ አሰልጣኞችና የእግር ኳስ ባለሙያዎች በዘንድሮው በዓለም ዋንጫው ተግባራዊ ለሆኑ ቴክኖሎጂዎች ጠቀሜታ ድጋፋቸውን እንደገለፁ፣ የሊግ አሰልጣኞች ማህበር በቅርቡ የሰራው ጥናት አረጋግጧል፡፡ በጥናቱ እንደተገለፀው ለዳኞች ውድድር የመምራት ብቃትን ለማሳደግ ተግባራዊ የሆኑት ቴክኖሎጂዎች በ20 አገራት የሚገኙ በተለይም በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚሰሩ አሰልጣኞች በእግር ኳስ ስፖርት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል 93 በመቶው ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡

19

እስከ ‹ሮቦት› ብሄራዊ ቡድን?

Saturday 2nd of August 2014 11:11:58 AM  |  Addis Admas Sport

         አንዳንድ ዘገባዎች በሚቀጥሉት 20 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ ስፖርት የሮቦት ዳኞች እና የሮቦት ተጨዋቾች ማሰለፍ የሚቻልበት የስልጣኔ ደረጃ ይመጣል ይላሉ፡፡ ምናልባትም የቴክኖሎጂ ድጋፍ አስፈላጊነቱ ከታመነበት ፊፋ የተርመጠመጠበትን የሙስና ችግር የሚያጋልጥ ቴክኖሎጂ ቢፈለሰፍ ብለው የማጣጣያ ትችት ያቀረቡ መረጃዎች፤ በሚቀጥሉት ሃምሳ ዓመታት ዓለም ዋንጫ በጨረቃ ላይ ሊስተናገድ ይችላል ብለው አሹፈዋል፡፡ኤችቲቢ ኤንድ ፊልቸር ቦነስ የተባለ ተቋም የዓለማችን የእግር ኳስ ስፖርት የወደፊት አቅጣጫዎች ብሎ በሰራው ምርምር ይፋ እንዳደረገው በሚቀጥሉት 50 ዓመታት ስፖርቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ለውጦች ማሳየቱ የማይቀር ይመስላል፡፡ ብዙዎቹ ቴክኖሎጂዎች እስከ 2022 እ.ኤ.አ ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚችሉም ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.