HEALTH /

Top

20

ፍርሃት ላለበት ሰው በፍፁም መንገር የሌለብን 5 ነገሮች

Wednesday 22nd of November 2017 01:30:18 PM  |  Fana Health

ፍርሃት ላለበት ሰው በፍፁም መንገር የሌለብን 5 ነገሮች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርሃት ማለትም ድንገተኛ በሆነ ክስተት በደቂቃዎች ውስጥ የሚፈጠር ከባድ ፍርሃት ውስጥ የሚገቡ ወይም ምቾት የሚያጡ ሰዎች አሉ።

እነዚህ ሰዎች ድንገት የልብ ምት መዛባት፣ የልብ ድካም፣ ማላብ እና መንቀጥቀጥን የመሰሉ ችግሮች ያጋጥማቸዋል። በተጨማሪም የትንፋሽ ማጠር ወይም መቆራረጥ ስሜቶች ያጋጥማቸዋል።

ለፍርሃት የተጋለጠው ሰው በምልክት እና በቃላት የሚገለፁ ምላሾችን ሊሰጥ እንደሚችልም ይነገራል።

በኒውታውን ፔንስይልቫኒያ የቡክስ ካውንት በአእምሮ ጭንቀት ማዕከል የህክምናው ዶክተር ሮኒት ሌቭይ እንደሚሉት፥ የፍርሃት ያለው ሰው ምክንያታዊ በሆነ መንገድ አንድ ነገር የማድረግ አቅሙ በመዳከሙ የተነሳ አእምሮው አደጋ ላይ ይወድቃል።

በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ የሚወዱትን ሰው ለመርዳት ከልብ የሚፈልጉ ከሆነ፥ ያልተለመዱ ምላሾችን በማራቅ በትክክለኛ መንገድ ማገዝ ይችላሉ ብለዋል የህክምና ባለሙያው።

በዚህም የአእምሮ ፍርሃት ላለበት ሰው መናገር የሌሉብን ነገሮች እንደሚከተለው ያስቀምጣሉ።

“መጨነቅህን አቁም”

ይህ ምክር ፍርሃቱ እንዲያቆም ሊያደርገው ይችላል፤ ነገር ግን የአእምሮ ፍርሃት ያለበት ሰው ይህን በሚሰማበት ጊዜ ሰውነቱ በአደጋ ላይ እንደሆነ በማሰብ የመኖር አማራጭ ይፈልጋል።

በዚያን ጊዜ ምክንያታዊው የአዕምሮ ክፍል ይዘጋና ስሜታዊ የአእምሮ ክፍል፥ የአንጎል ማእከሉ ራሱን መቆጣጠር ይጀምራል። ይህም የአእምሮ ክፍሉ በምክንያታዊነት ከማያስባቸው ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ይችላል ነው ያሉት ዶክተር ሌቭይ።

“ጥሩ ነው ያለኸው”

የምትወዱት ሰው ከአእምሮ ፍርሃት በተነሳ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶበት ሁኔታው ደህና አይደለም። ይህ ሁኔታም ከእራሱ ጋር ጦርነት እንደጀመረ የሚያሳይ ጭንቀት ይታይበታል።

በተጨማሪ የውጭ ሁኔታው ስትታዘቡትም ጭንቀት እንዳለው የሚያሳዩ ምልክቶች ይታዩበታል።

በዚህ ጊዜ ጥሩ ወይም ደህና ነህ ያለኸው ካልነው በጭንቀት ለተያዘው ሰው ይህ ትንሽ እፎይታ ሊሰጠው ካልሆነ በስተቀር ከችግሩ ሊያወጣው አይችልም።

“ተረጋጋ”

ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ተቋም እንደገለፀው የአእምሮ ፍርሃት በድንገት የሚያጋጥም ሲሆን፥ ለብዙ ደቂቃዎች ሊቆይ ይችላል።

ብዙውን ጊዜ የአእምሮ ፍርሃትን የሚታይበት ሰው ከሐኪም ጋር የመቋቋም ችሎታ ይማራል፤ ነገር ግን ጣልቃ በመግባት ድንገተኛ አደጋውን ማስቆም በጣም ከባድ ነው ሲሉ ዶክተር ሌቭይ ይገልፃሉ።

ስለዚህ አንድ ሰው ጭንቀቱ በቀላሉ እንዲተወው መረጋጋት የሚያስችሉ ቃላትን ተጠቅሞ መምከር ያስፈልጋል።

“አትጨነቅ”

በአእምሮ ፍርሃት ውስጥ ያለው ሰው ከችግሩ እንዲወጣ በማሰብ፥ "ስለሱ አትጨነቅ" ወይም "ስለሱ አታስብ" የሚል ትዕዛዝ መስጠት የበለጠ ፍርሃቱን ሊያባብስ ይችላል።

ባለሙያው እንደሚሉትም፥ እንደነዚህ ያሉ ቃላት መናገር በአእምሮ ተቃራኒ የሆነ ውጤት ሊያመጣ ይችላል።

“ጠንከር በል”

አንድ ሰው ጠንካራ እንዲሆን የምንሰጠው ምክር፥ መልእክቱ ምናልባት ግለሰቡ ደካማ ወይም ስሜቱን መቆጣጠር እንደማይችል ሊያመላክት ይችላል፤ ይህም ችግሩን የበለጠ ያባብሷል።

ከጊዜ በኋላም እንደዚህ ያለ ምክር በጭንቀት እና በስጋት ላይ ከሚኖር ሰው ጋር ያለንን ግኑኝነት በመጉዳት ወዳጃችን እንደማንረዳው ሊሰማው ይችላል ነው የተባለው።

ምንጭ፦www.health.com

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.