HEALTH /

Top

20

የሃሳብ ሙግትን ለማሸነፍ የሚረዱ ነጥቦች

Tuesday 5th of September 2017 09:40:06 AM  |  Fana Health

የሃሳብ ሙግትን ለማሸነፍ የሚረዱ ነጥቦች

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 30 ፣ 2009 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) አለመግባባትና አለመስማማት በህይዎት ውስጥ ትልቁ ስሜትን የሚፈታተን ጉዳይ ነው።

አንዳንድ ሰዎች አለመግባባቶችን ለማስወገድ ረዥምና ማንኛውንም መንገድ ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

በአንጻሩ ሌሎች ደግሞ ከዚህ በተቃራኒው ከጉዳዩ ጋር መቆየትን ይመርጣሉ፥ ሁለቱም የራሳቸው አካሄድ ቢኖራቸውም አለመስማማትና አለመግባባቱ ግን በምንም መንገድ አዋጭነት የለውም።

ትልቁ ጉዳይ ግን አለመግባባትና ግጭትን እንዴት መፍታት ይቻላል የሚለው ይሆናል።

በዚህ አለመግባባትና አለመስማማት መሃል በራስ ሃሳብ ማሸነፍና የራስን እሳቤ በሰዎች ውስጥ ለማስረጽ ጠንካራ ስነ ልቦናና ሰፊ ዝግጅት ያስፈልጋል።

ከዚህ አንጻርም በሚኖር የሃሳብ ክርክር መሃል የራስን ሃሳብ እንዴት በሰዎች ውስጥ ማስረጽና የሃሳብ ሙግትን ማሸነፍ እንደሚቻል ማወቁ ጠቃሚ ነው።

የስነ ልቦና ባለሙያዎች ደግሞ የሃሳብ ሙግትን ማሸነፍ የሚቻልባቸውን ነጥቦች ይጠቅሳሉ።

እውነታውን መረዳት፦ በአንድ ሃሳብ ላይ ከሆነ ሰው ጋር እየተከራከሩ የሃሳብ ልዩነት ሊፈጠር ይችላል።

ይሁን እንጅ ይህን የሃሳብ ልዩነት ለመፍታትና ትክክለኛውን ሃሳብ ለማስረጽ ግን ከስሜት በጸዳ መልኩ እውነታውን መያዝ በዚያ መርህ ላይ ተመስርተው ሊከራከሩ ይገባል።

ላለመሸነፍና የእኔ ሃሳብ ብቻ ነው ትክክል በሚል ግትር አቋም በመያዝ ከእውነታው ወጣ ባለ መልኩ የራስን ሃሳብ በሰዎች ላይ ለማስረጽ መሞከር ግን፥ አሸናፊነት ሳይሆን ተሸናፊነት መሆኑንም የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የሌሎችን ሰዎች እሳቤ ለማየትና ለማድመጥ መዘጋጀት፦ የባላንጣዎን እሳቤ ለማወቅና ለመረዳት በሚል መስማማትና መግባባት አይጠበቅብዎትም።

ከዚህ በተቃራኒው ግን የሃሳብ ልዩነቶችን በማሸነፍ የራስዎን እሳቤ ማስረጽና ተቀባይ ማድረግ ከፈለጉ፥ ያሉበትን አለም ሁኔታ ባላንጣየ ወይም ተገዳዳሪየ በሚሏቸው ሰዎች እይታ ማየትና መረዳት።

ተቃራኒየ ወደ ሚሏቸው ሰዎች እሳቤ አተያይና እሳቤ ይበልጥ ቀረብ ብለው ነገሮችን ለማወቅ መጣርዎ፥ እነርሱን ምን አይነት ነገር ጫና እንደሚፈጥርባቸውና እንደሚያሸንፋቸው ለማወቅም ይረዳወታል።

ነገሮችን ለመቀበል መዘጋጀት፦ የሃሳብ ልዩነትን ለማስታረቅ በሚሞግቱበት ወቅት እኔ ብቻ ትክክል ነኝ ብሎ ግትር አቋም መያዙ በፍጹም አይመከርም።

በዚህ ወቅት ባላንጣየ ለሚሉት ሰው ሌሎች አማራጮችን ሳይመለከቱ በደፈናው የሃሳብ ልዕልናዎን ለማረጋገጥ እየሞከሩ እንደሆነ ማሳየቱም መልካም አይደለም።

ከዚያ ይልቅ የእርስዎ ተቃራኒ ሆነው ለቀረቡ ሰዎች ሃሳብ ቦታ እንዳለ ማሳየትና ልዩነቶችን ማስማማትና ማቻቻል የሚቻልበትን መንገድ በማሳየት ወደ ራስዎ ሃሳብ ለማቅረብ መሞከር።

ተቃራኒዎችዎንም ለእነርሱ ሃሳብና ምልከታ ቦታ እንዳለ ሲያውቁ የእርስዎን ሃሳብ በማጋራት ብቻ አጋርዎ ማድረግ ይችላሉ።

ስሜታዊ አለመሆን፦ ስሜትን መቆጣጠር መቻልና ከስሜት በጸዳ መልኩ መወያየት መቻል በክርክር ወቅት ቀዳሚው መሆን መቻል አለበት።

በስሜታዊነት ከቀረቡ ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን የመጦዝም ሆነ ፍሬ አልባ የለዘበ ክርክር የመሆን እድሉም ከፍተኛ ነው።

በጣም ስሜታዊ ሆነው አካላዊም ሆነ የገጽታ መለዋወጥ በታከለበት ሁኔታ መከራከሩ ከመግባባት ይልቅ ነገሩን ማደፍረስ ይጀምራል።

ከዚህ በተቃራኒው ሆነውም ፍጹም ትሁትና በመሰላቸት አይነት ስሜት ውስጥ ሆነው ክርክሩን ማድረግዎም ለእርስዎ አይጠቅምዎም።

ከዚያ ይልቅ በሰከነ መንፈስ ነገሩን በማየት መከራከርና ሃሳብዎን በማሳየት ለማሸነፍ መመሞከሩ የተሻለም ይሆናል።

ልዩነቱ ሊፈታ እንደሚችል ማሰብ፦ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ዘወትር በዚህ መሰል ሁኔታ ውስጥ ሲገቡ ልዩነቱ ተፈቶ በሃሳብ እንደሚግባቡ ማሰብን ይመክራሉ።

በዚህ መንፈስ ሆነው ሃሳብን ለማስታረቅ በሚሞክሩበት ጊዜ ቀና መንገዶችን የማየት እድልዎም በዚያው ልክ ከፍ እንደሚልም ያነሳሉ።

ከዚህ አንጻርም ለልዩነቶች ማስታረቂያ መንገድ አግኝተው መፍታት እንዲችሉም በር ይከፍታል።

ዘወትር ከሆነው ነገር ገለል ብሎ ነገሮችን የማየት ልማዱን በደንብ ለማዳበር ነገሮችን በቀና መንገድ መጀመሩ ይመከራል።

ባላንጣን ማክበር፦ ባለመግባባትና ባለመስማማት የሚደረጉ ክርክሮች ብዙ ጊዜ በሚያስማማ መልኩ አሸናፊ አይኖራቸውም።

ሁለቱም ወገኖች ለድርድር የተቀመጡበት ግንኙነትን ማስቀጠል አልያም የተፈጠረን ችግር የመፍታቱ ነገር መቋጫ ቢያገኝም፥ በራሳቸው መንገድ መልካም ነገር እንዳገኙ ያስባሉ በራሳቸው መንገድም አሸናፊዎች ሊሆን ይችላሉ።

ከዚህ ባለፈ ግን ባላንጣ ሆኖ የቀረበን ሰው ከዚህ በኋላ ማግኘት ባይፈልጉ እንኳን፥ ክብር አለመስጠትና ማጥላላት ፍጹም ስህተት ነው።

ቢያንስ በነበረው የሃሳብ ፍጭት ግላዊ ሳይሆን የሆነ ሁኔታን እልባት ለመስጠት ሲባል ብቻ በተቃራኒነት እንደቆማችሁ ማሰብና ከዚያ በኋላ ያለውን ታሪክ ለማድረግ መሞከር።

ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በህይዎትዎ ወስጥ የሚያስተናግዷቸውን ልዩነቶች ለመፍታትና ለማስታረቅ ይጠቀሙባቸው።

 

 

 

 

 

 


ምንጭ፦ psychologytoday.com

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.