HEALTH /

Top

20

ቢ12 ምንድን ነው፤ በበቂ ሁኔታስ እያገኘን ነው…?

Tuesday 5th of September 2017 07:30:13 AM  |  Fana Health

ቢ12 ምንድን ነው፤ በበቂ ሁኔታስ እያገኘን ነው…?

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቢ12 (B12) ቫይታሚን ሲሆን፥ ሰውነታችን ቀይ የደም ህዋሶችን እና ዘረመሎችን እንዲያመርት የሚረዳ እንዲሁም በርካታ ጠቀሜታዎች ያለው ቫይታሚን ነው።

የሚያስፈልገን የቫይታሚን ቢ12 መጠን እንደ እንድሜያችን፣ አመጋገባችን፣ የምንወስደው የመድሃኒት አይነት እና የጤና ሁኔታ መሰረት ሊለያይ ይችላል።

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ቀይ የደም ህዋሳችን ጤናማ ባልሆነ መልኩ እንዲያድግ በማድረግ ህዋሱ የሚጠበቅበተን ስራ በአግባቡ እንዳይሰራ ያደርጋል።

ቀይ የደም ህዋሶች ሄሞግሎቢንን በመጠቀም ኦክሲጅን በሰውነታችን ወሰጥ አንዲዘዋወር የሚያደርጉ ሲሆን፥ ህዋሶቹ ስራቸውን በአግባቡ መስራት ካልቻሉ ለደም ማነስ እና መሰል የጤና እክሎች ይዳርጉናል።

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ምልክቶች

ቫይታሚን ቢ12 በሰውነታችን ውስጥ በርካታ ጠቃሚ ነገሮችን የሚሰራ ሲሆን፥ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ካጋጠመን ግን፦

• ከመጠን ያለፈ የሰውነት መዛል፣ የትንፋሽ ማጠር እና የተዛባ የልብ ምት

• የጉልበት ማነስ ወይም ራስን መሳት

• የአፍ ውስጥ እና የጉሮሮ ህመም እንዲሁም ምላሳችን ቀይ መሆን

• የጡንቻ መዛል

• የእይታ መረበሽ (እይታ ላይ ብዥታ መፈጠር) እና ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት

• ድብርት እና የባህሪ ለውጥ

• ግራ መጋባት (መወዛገብ)

• ነገሮችን ከማስታወስ እና ቶሎ ከመረዳት ጋር ችገር መፈጠር

• የምግብ ፍላጎት እና የሰውነት ክብደት መቀነስ እንዲሁም የሆድ ድርቀት ሊያጋጥመን ይችላል።

እነዚህ ምለክቶች ቀስ በቀስ እየተስፋፉ የሚመጡ ሲሆን፥ ምልክቶቹ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያሉ መለየት አይቻለም።

እንዲህ አይነት ምልክቶች የሚስተዋሉብን ከሆነ ግን የጤና ባለሙያን ማማከር እና በአፋጣኝ ህክምና ማግኘት ይኖርብናል።

ለረጅም ጊዜ የቆየ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ከበድ ያለ የጤና እክል ያስከትላልም ተብሏል፤ ከእነዚሀም ወስጥ፦

• የነርቭ ስርዓታችን ላይ ችግር ማስከተል

• ጊዜያዊ የመካንነት ችግር

• የልብ ችገር

• አስቸጋሪ እርግዝና እና ጤናማ ያልሆነ ልጅ እንዳይወለድ ማድረግ ይገኝበታል።

የቫይታሚን በ12 እጥረት ምከንያቶች

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት በተለያዩ ምክንያቶች ይክሰታል፤ ከእነዚህም ወስጥ፦

• በምንመገበው ምገብ ውስጥ የቫይታሚን ቢ12 በበቂ ሁኔታ አለመኖር

• አልኮል በእዝቶ መጠጣት

• የሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት መዛባት ተጠቃሽ ናቸው።

ህክምና

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ህከምና በጤና ባለሙያዎች የሚካሄድ ሲሆን፥ ይህም ባለሙያዎቹ በደማችን ውስጥ ያለውን የቫይታሚን ቢ12 መጠንን በመለካት ይለያሉ።

በዚህም የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ምልክቶች ከታየብን ለሁለት ሳመንታት በየቀኑ በመርፌ የሚሰጥ የቫይታሚን ቢ12 መወጋት ይኖርብናል።

ከዚህ በመቀጠልም እጥረቱ እንዲከሰት ያደረገው ምክንያት ላይ በመመርኮዝ ከሚዋጥ መድሃኒት ጀምሮ ሌሎችም ህከምናዎች ሊደረጉልን ይችላሉ።

ከዚህ ውጪ ግን አመጋገባችንን ማስተካከል እና በቫይታሚን ቢ12 የበለፀጉ መግቦቸን አዘውትሮ መመገብ እጥረቱን ቀድሞ ለመከላከል ያስችለናል።

ቫይታሚም ቢ12 ንጥረ ነገርን ከያዙ ምግቦች ወስጥም፦

ስጋ፣ አሳ፣ እንቁላል እና ወተት ይገኙበታል።

የእንሰሳት ተዋዕጾዎችን የማይመገቡ ሰዎች ከጥራጥሬዎች የተሰሩ ቁርስ ላይ አዘውትረን ለመመገብ መሞከር ይመከራል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co

 

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.