HEALTH /

Top

20

በኮንጎ ገጠራማ አካባቢ ተጣብቀው የተወለዱ ህፃናት ከፈታኝ ጉዞ በኋላ በቀዶ ህክምና ተነጣጥለዋል

Monday 16th of October 2017 10:40:07 AM  |  Fana Health

በኮንጎ ገጠራማ አካባቢ ተጣብቀው የተወለዱ ህፃናት ከፈታኝ ጉዞ በኋላ በቀዶ ህክምና ተነጣጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ገጠራማ አካባቢ በእምብርታቸው ተጣብቀው የተወለዱትን ህፃናት ቀደ ቀዶ ህክምና ማዕከል ለማድረስ ፈታኝ ጉዞ ቢደረግም ህፃናቱ በህይወት ተርፈው ህክምናው በስኬት ተከናውኗል።

ህፃናቱን በቀዶ ህክምና ለመነጣጠል የሚያስችለውን ህክምና ለማግኘት ወላጆቻቸው ከተወለዱ አንድ ሳምንት እድሜ ላይ የሚገኙትን ጨቅላዎች በሞተር ብስክሌት ጀርባ አድርገው ለ15 ሰዓታት የገጠር መንገድ ለመጓዝ ተገደዋል።

ከፈታኙ ጉዞ በኋላም በዋና ከተማዋ ኪኒሻሳ ደርሰው በጎ ፈቃደኛ ቀዶ ሃኪሞች የሚያስፈልገውን ህክምና አድርገውላቸዋል።

በ7 ወር እርግዝና ተወልደው የአንድ ሳምንት እድሜያቸው ላይ የሚገኙት ሴት መንታ ህፃናት 1 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለውን ጉዞ በአየር፣ በጫካ፣ እና ለአደጋ አጋላጭ በሆኑ መንገዶች ተጉዘው ነው በህይወት የተረፉት።

twinsinvillage.jpg

አኒክ እና ደስቲን የሚባሉት ሁለቱ ህፃናት በእምብርታቸው ተጣብቀው የተወለዱ ሲሆን በሌላ የሰውነት ክፍል አይጋሩም።

በገጠር አካባቢ ተጣብቀው ከሚወለዱ 200 ሺህ ህፃናት መካከል አንዱ ብቻ በህይወት የመቆየት እድል እንዳለው ጥናቶች ይገልፃሉ።

ሆኖም አኒክ እና ደስቲን በምዕራብ አፍርካዊቷ ሀገር ምንም ዓይነት የህክምና አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባት የሙዞምቦ ገጠር መንደር ተወልደው በህይወት ይገኛሉ።

ወላጆቻቸው ክላውዲን ሙኬና እና ዛይኮ ሙንዛዲ ተጣብቀው የተወለዱትን ልጆቻቸውን በቅርብ አለ ወዳሉት የህክምን ማዕከል ለመድረስ ሰፊውን ጥቅጥቅ ጫካ አቆራርጠው ለመሄድ ተገደዋል።

ከቀናት ጉዞ በኋላም በአንዲት ትንሽ ከተማ ደርሰው ልጆችን ለመነጣጠል የሚያስችለውን ህክምና ለማድረግ የገቡበት ሆስፒታል መሳሪያ እና ልምድ የሌለው በመሆኑ ወደ ሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪኒሻሳ እንዲሄዱ አዘዘ።

ከትንሿ ከተማ ተነስተው ኪኒሻሳ ወደሚገኘው የቫንጋ ሆስፒታል ለመድሯስ ደግም የግዴታ 300 ማይል ወይም ከ482 ኪሎሜትር በላይ መንገድን በፈታኝ ሁኔታ መጓዝ ሊጠበቅባቸው ነው።

ይህን የተገነዘበ አንድ ግብረሰናይ ድርጅትም በራሱ አውሮፕላን አማካኝነት ገጠራማውን የኮንጎ አካባቢ አቆራርጦ ኪኒሻሳ አደረሳቸው።

በከተማዋ ውስጥ ወደሚገኘው ቫንጋ ኢቫንጀሊካል ሆስፒታል ገብተው የህክምን ሂደቱን ጀመሩ፤ በቀዶ ህክምናም ህፃናቱ በስኬት እንዲነጣጠሉ ተደረጉ።

ለህፃናቱ የህክምና ክትትል እያደረገ የሚገኘው ዶክተር ጁኒየር ሙጂ በህፃናቱ ህይወት መትረፍ መገረሙን ተናግሯል።

በ37 ሳምንት የእርግዝና ጊዜ ውስጥ ተጣብቀው በህይወት እና በተፈጥሯዊ ሁኔታ የሚወለዱ ህፃናት በህይወት መኖራቸውን ስሰማ የመጀመሪያየ ነው ብሏል።

አሁን ላይ ህፃናቱ የሚሰጣቸውን አልሚ ምግብ በአግባቡ እንደሚወስዱ፣ እንደሚተኙ በአጠቃላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ነው ሃኪሙ የተናገረው።

ለሶስት ሳምንታትም ተገቢውን የህክምና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው እና ወደመጡበት የገጠር አካባቢ እንደሚመለሱ ጠቁሟል።

ዶክተር ሙጂ እንዳለው ከሆነ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጣብቀው የተወለዱ ህፃናትን በቀዶ ህክምና በስኬት መለያየት ሲቻል ይህ የመጀመሪያ ነው።

 

 

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.