HEALTH /

Top

20

በቀን ውሎዎ ውጤታማ ለመሆን የሚረዱ የማለዳ ልማዶች

Monday 19th of June 2017 08:00:07 AM  |  Fana Health

በቀን ውሎዎ ውጤታማ ለመሆን የሚረዱ የማለዳ ልማዶች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ማለዳ ተነስተው የሚከውኗቸው ማንኛውም ነገሮች በቀን ውሎዎ ውስጥ የራሳቸው አወንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተዋጽኦ አላቸው።

ቀኑን በተዛባና ባልተገባ አካሄደ ከጀመሩት አስደሳች ያልሆነ ቀን ማሳለፍዎ አይቀርም፥ በተቃራኒው ሲሆን ደግሞ መልካም ጎኖች ይኖሩታል።

ከፈጠራ ብቃት እና ውጤታማነት ጋር በተያያዘ የሚሰሩት የስነ ልቦና ባለሙያዋ ኤለን ጉድዊን ደግሞ በውሎዎ ስኬታማና ውጤታማ ለመሆን የሚረዱ ያሏቸውን ምክረ ሃሳቦች ይዘረዝራሉ።

እቅድ ማውጣት፦ ቀጣዩን ቀን ከመጀመርዎ በፊት በቅድሚያ መከዎን ያለበዎት ነገር ስለሚያሳልፉት ቀን እቅድ ማውጣትና ፕሮግራም ማዘጋጀት ነው።

የዛሬ ውሎዎን ከውነው ሲጨርሱ ማታ ወደ ቤት በሚያመሩበት ወቅት ነገ በዋናነት የሚከውኗቸውን ተግባራት መለየትና መዘርዘር፥ ከዚህ ባለፈም የቀኑን የመጀመሪያ ሰዓታት በምን መልኩ እንደሚያሳልፉ መወሰን።

ውሃ መጠጣት፦ ማለዳ ሲነቁ ከሎሚ አልያም ከበረዶ ጋር ቀላቅለው ቀዝቀዝ ያለ ውሃ መጠጣት ሰውነት በምሽት ያጣውን ፈሳሽ በአግባቡ በመተካት የተስተካከለ የምግብ መንሸራሸርና መፈጨት ስርዓቱን እንዲሰራ ያደርገዋል።

ከዚህ ባለፈም የፈሳሽ እጥረት በአዕምሮ ስራ ላይ ያለውን አሉታዊ ጎንም ማስወገድ ይችላሉ።

ተመስጦ፦ የተወሰነ ጊዜ ተመስጦ ማድረግ አዕምሮ የፈጠራ አቅሙን ይበልጥ እንዲያሳድግና እንዲያጎለብት ይረዳዋል።

ይህን ማድረጉ ትኩረትን በመሰብሰብ አዕምሮ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራና የፈጠራ አቅሙ እንዲጨምር ያደርጋል፤ ይህ መሆኑ ደግሞ በሚከውኑት ስራ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖርዎት ያግዛል።

ፀጥ ባለ ቦታ ሆነው የተወሰነ ጊዜ በትኩረት በመመሰጥ በዕለት ውሎዎ የተሻለ መፈጸምና መከወን ይችላሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ ቀኑን በሙሉ ሃይል ለመዋልና ያለ ድካም ለመስራት በማለዳው ጊዜ የተወሰነ መንቀሳቀስና ሰውነትን ማዝናናት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በከወኑ ቁጥር ለሰውነትና ለአዕምሮ ንቃት የሚያግዙ ሆርሞኖች በሰውነት በብዛት ይመነጫሉ።

እነዚህ ሆርሞኖች የድካምና መጫጫን ስሜትን በማስወገድ ሰውነትዎ ዘና እና ነቃ እንዲል የሚያግዙ ናቸው።

ማለዳ ተነስተው የእግር ጉዞና ሽርሽር ማድረግ አልያም ሩጫ መሮጥም ለዚህ ይረዳወታል፤ ይህን ማድረጉ አዕምሮ በተሻለ ንቃት እና የፈጠራ ብቃት እንዲሰራ ያስችለዋል።

የማለዳ ፀሃይ፦ እንቅስቃሴ የሚያደርጉም ከሆነ በተቻለ መጠን ንጹህ የማለዳ አየርና ፀሃይ በሚያገኙበት ከቤት ውጭ ቢሆን ይመረጣል።

ማለዳ ሰውነትዎ የፀሃይ ብርሃን አገኘ ማለት አዲስ የስራ ቀን እንዳለ ራስዎን ለማዘጋጀት ይጠቅምዎታል።

የተደረጉ ጥናቶችም ከአንቅልፍዎ ሲነቁ የፈካች ፀሃይ ወይም ብርሃን ሲያዩ ሰውነትዎ ለመተኛት የሚያግዘውን ሆርሞን ማመንጨት በማቆም የተሻለ ንቁ እንዲሆን ያግዘዋል።

እናም ማለዳ በተፈጥሮ በምትፈካው የፀሃይ ብርሃን በመታገዝ በቀን ውስጥ ከሚከሰት የስሜት መለዋወጥና ድብርት ራስዎን መታደግ እንደሚችሉም ባለሙያዎች ያነሳሉ።

ዘወትር በስሜት መቀያየርና መረበሽ የሚቸገሩ ሰዎችም ማለዳ ተነስተው የፀሃይ ብርሃን ባለበት ቦታ የእግር ጉዞ ቢያደርጉ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

ቁርስ መመገብ፦ ምግብ ለሰውነት የሃይል ምንጭ ነው፤ እናም ማለዳ ቁርስ ተመግቦ መውጣት ሰውነት በቀን ውሎው የተሻለ ብርታት እንዲያገኝ ይረዳዋል።

በዚህ ወቅት መመገብዎ ሰውነት ለሃይል እና ብርታት የሚረዱትን ንጥረ ነገሮች እንዲያገኝም ይረዳዋል፤ ማለዳ መመገብ ደግሞ ሰውነት ያገኘውን ምግብ ወደ ሃይል የሚቀይርበትን መልካም አጋጣሚም ይፈጥርለታል።

ጠዋት ላይ ሳይመገቡ ከቀሩ በከሰዓት የምሳ ወቅት አብዝተው እንዲመገቡ በማድረግ በከሰዓት የስራ ውሎዎ ዘና ብለው እንዳይሰሩ የማድረግ አቅም አለው።

 

የቁርስ ጠቀሜታ አዕምሮ በሙሉ ሃይሉ ወደ ስራ እንዲገባ ያግዘዋልና ይጠቀሙበት።

ከዚህ ባለፈ በቀን ውስጥ የሚያደርጉትን አጭር የዕረፍት ጊዜ (ናፕ) መቀነስም ለቀን ውሎዎ ውጤታማነት መልካም መሆኑን ባለሙያዋ ያነሳሉ።

ይህን መሰሉ ልማድ በጊዜ ሂደት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝንም ይገልጻሉ።

ይህን ልማድ ማድረጉ ዘወትር በዛ ሰዓት ከስራ ይልቅ ወደ እረፍት ማምራትና በቀሪው ጊዜም የድካምና የመጫጫን ስሜትን ያጎለብታል ይላሉ።

ማለዳ ቤት ውስጥ ቡና አልያም ሻይ ነገር አዘጋጅቶ ከቁርስ በኋላ መጠቀምን መልመድ።

ቤተሰብና ከጓደኞችዎ ጋር ቁርስዎን ተመግበው ወደ እለት ተግባርዎ ቢያመሩ የተሻለ ይሆናል።

የእኔ ከሚሏቸው ሰዎች ጋር ይህን መከዎኑ ዘና የማለት ስሜትን ለማዳበርና የተሻለ ብርታት ለማግኘትም ይረዳልና ይህንኑ ይከውኑ የባለሙያዋ ምክር ነው።

 

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ nbcnews.com

                   


Save for Later/ በኋላ ለማንበብ ያስቀምጡ
   
Up vote :20     Down vote :0     Ajeb vote :20

    Ajebnew Email

    Subscribe to ajebnew email for daily, weekly and/or monthly feeds and everything worth your time will be right in your inbox!


    WE ARE STORYTELLERS. BE SURE TO NEVER MISS ANYTHING.